አንዴ አረብ ሊግ፤ አንዴ G7፤ አንዴ ዩሮፒያን ዩኒየን፤ አንዴ አሜሪካ፤ አንዴ ግብጽና ሱዳን፤ ይሄም አልበቃ ብሎ፤ የክልል አፈንጋጭና ጎረምሶች፤ ገና በሱ ሲገርመን የአለም ድርጅቶችና ሚዲያዎች፤ ያም አልበቃ ብሎ፤ የእናት ጡት ነካሾች የሆኑ ባንዳዎች በዩትዩብና በፌስቡክ ... ደሀውን ሕዝብ፤ ሊያባሉ፤ ሲጮሁብሽ ..... ወይ ኢትዮጵያ !!! ምነው ግን ጠላቶችሽ በዙ? በዛም ሆነ በዚህ ዋጋውን የሚከፍለው ደሀው ሕዝብ ነው። በፊት በቀን ግማሽ እንጀራ ብቻ የሚበላውን ደሀ፣ በመአቀብና በጦርነት፤ አፈር ለማስበላት ነው? ግን ለምን ቀኑብሽ? እንደ ዮሴፍ ያለምሽው ሕልምሽ አስፈርቷቸው ይሆን? ኧረ የዳዊትና የዮሴፍ አምላክ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ፤ አንተው በቃ በለን፤ አንተ ተዋጋልን። እንደ ጎልያድ፤ ባላቸው ሀይል ሀብትና ጉልበት ተማምነው የተነሱብንን፤ ልታቆምልን ትችላለህ። እኛም፤ ትናንት ሊበሉን እና ሊያጥህፉን በተነሱት ላይ እንደረዳኧን፤ አንተን ተማምነን እንቆማለን። ዮሴፍንም በውሸት ምስክር ወደ ጥልቁ የጣሉትን ፤ በእግሩ ስር እንዳደረክና ልክ እንደ ሕልሙ፤ እሱን የበላይ የጠሉትን የበታች እንዳደረክ፤ ... ስምህን እንጠራለን ከመከራችንም እንድናለን ተብሎ እንደተፃፈ፤ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ፣ ብለን ሕዝቦችህ፣ አብዝተን እንጮሀለን።
top of page
bottom of page