ክሬዲት (credit) ዶ/ር አብይ አህመድ ፡- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር
ምንጭ (Source) https://www.facebook.com/112704996810839/posts/627197308694936/?d=n
ኢትዮጵያዊነት ማለት . . .
ግዙፍ ነው እንደዋርካ፤
ሰማዩን የጠቀሰ
ዳመናውን የነካ፤
ሥሩ መሰረት የያዘ
ቅጠል-አበባው የፈካ፤
ቅርንጫፉ የሰፋ፣ ግንዱ ጸንቶ የኖረ
ቅርፊቱ የደነደነ፣ ዘመናትን የተሻገረ።
ኢትዮጵያዊነት ማለት . . .
የመንፈስ ጣራ ከፍታ
ሁሉን ሰብሳቢ ገበታ
ለቀመሰው አንጀት አርስ
ሲኦል በመውረድ የማይፈርስ።
ህልውናውን በአንድነቱ
በራሱ አቅም የሚያጸና፤
በወጀብ የማይናወጥ
የማይሰበር ቁመና ፤
በእሳት በፍም የተፈተነ
በችግር ሚዛን የተመዘነ
የማንነት ሥሪቱ፣
የባህል፣ የወግ እሴቱ፣
በሳሌም ፍቅር እንዲኖር - ከአልፋ እስከ ኦሜጋ፤
የተሸመነ ረቂቅ ጥበብ - ጃኖ ነው የነፍስ የሥጋ።