Credit: Dr. Abiy Ahmed - Prime Minister of Ethiopia Source: ፋና ብሮድካስቲንግ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን ህዝብ ያለንን ድጋፍ በሙሉ ልብ እናረጋግጣለን ሲሉ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲውተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን ወደ ዲሞክራሲ የሚያርጉት ሽግግር በርካታ ተግዳሮቶች እየገጠሙት መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ወንድም የሱዳን ህዝብ እና መንግስት የገጠመውን ወቅታዊ ችግር በቅርበት እየተከታተለው ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።
ይህን ወቅታዊ ችግርም ሱዳናዊያን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በራሳቸው እንደሚፈቱት እናምናለን ብለዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችንና ፈተናዎችን በመጠቀም የውጭ ክፉ ኃይሎች በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባትና ብሔራዊ ሉዓላዊነታችንን በመጣስ የእነሱን የበላይነትእንዲሁም ፍላጎታቸውን ለመጫን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም እያየን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
በመሆኑም ሱዳን በምንም መልኩ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ፣ ግልጽ እና የተደበቁ ትዕዛዛትን መፍቀድ የለባትም ብለዋል።
የኢትዮጵያ አጀንዳም የሚመነጨው ከሁለቱ ህዝቦች የቆየ ወንድማማቻዊ ትስስር መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ የሱዳን ህዝብ እና መንግስት የተጋረጡባቸውን ችግሮች እና ፈተናዎች የማለፍ ብልሃቱና ጥበቡ እንዳለው እምነታችን የፀና ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
コメント