top of page

በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ ቆይተዋል ያላቸውን የውጭ ሃገር ዜጎች በ72 ሰዓታት ከሀገር እንዲወጡ አዘዘ

Writer's picture: Endalk TessemaEndalk Tessema

Credit: Fana Brodcasting


መንግስት በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ ቆይተዋል ያላቸውን የውጭ ሃገር ዜጎች በ72 ሰዓታት ከሀገር እንዲወጡ አዘዘ


አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትዮጵያ የዓለም ህጻናት አድን ድርጅት ጽህፈት ቤት (ዩኒሴፍ) እና በተመድ የሰብዓዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነት ሲሠሩ የነበሩ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ሥራ ሲሠሩ የተገኙ የውጭ ሃገር ዜጎች በ72 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ መታዘዙን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ከዩኒሴፍ ተወካይ በተጨማሪ ከሀገር እንዲወጡ የተወሰነባቸው ግለሰቦች፥ በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ እየሠሩ ያሉ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አብራርቷል፡፡


በዚህም መሠረት ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ ከተሰጠባቸው የውጭ አገራት ዜጎች መካከል ሚስ አደል ኮድር በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ ይገኙበታል፡፡


በኢትዮጵያ ከዩኒሴፍ ሃላፊዋ በተጨማሪ፥ ከሃገር ውስጥ እንዲወጡ ከተወሰነባቸው ግለሰቦች መካከል በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ምክትል አስተባባሪ የሆኑት ሚስ ጋዳ አል ጣሂር ሙዳዊ ይገኙበታል፡፡


በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ አገልግሎት አስተባባሪና ቋሚ ተጠሪ ጽህፈት ቤት የሰላምና ልማት አስተባባሪ የሆኑት ሚስተር ኪዌሲ ሳንስክሎቴ እንዳሉበት ታውቋል፡፡


በተጨማሪም ሚስተር ሳኢድ ሞሐሙድ ሔርሲ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ኃላፊ እንዲሁም ሚስተር ግራንት ሊቴ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ አገልግሎት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የሰብዓዊ ድጋፍ ምክትል አስተባባሪ ተጠቅሰዋል፡፡


የኢትዮጵያ መንግስት ከድርጅቶቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማጤን እንደሚገደድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል፡፡


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡


ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!





21 views0 comments

Opmerkingen


Post: Blog2 Post

Subscribe Form

Thanks for submitting!

©2021 by Ethiopianz. Proudly created with Wix.com

bottom of page